Work

ማህበራዊ ፍትህን ለማጎልበት የሚያግዙ ዘመን ተሻጋሪ የልማት አካሄዶች፡- የ“እረኛዬ” ድራማ ጭብጣዊ ትንታኔ

Year: 2026
Type: article
Abstract: በዓለም ላይ የሥነ ጽሑፍዘውጎችን የሚመረምሩ ጥናቶች እየተበራከቱ የመጡ ቢሆንም፣ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ተከታታይ ድራማዎችን ጉዳይ ይዘው የሚነሱቱ ግን ውስን ናቸው። እነዚህንና መሰል ክፍተቶች መነሻ በማድረግ፣ ይህ ጥናት ከእረኛዬ ድራማ የተገኙ ማህበረሰባዊ ፍትህን ለማጎልበት የሚያግዙ አካሄዶችን ይዳስሳል፡፡ ከአጠናን ዘዴ አኳያ ጥናቱ የተመሰረተው ፍጹም አይነታዊ (pure qualitative) በሆነ ውስን የጥናት ዘዴ ሲሆን የይዘታዊ ትንተና (content analysis) በመጠቀም በድራማው ውስጥ አሉ የተባሉ አበይት ጭብጦች ላይ ትኩረት ተደርጓል። በአራት ምዕራፎች ከተዋቀሩባቸው 48 የድራማው ክፍሎች ላይ 29 ክፍሎች ታላሚ የናሙና ስልት በመጠቀም ተመርጠዋል። የድራማው እምቅ ጭብጦች እና የተንጸባረቁባቸው መንገዶች በይዘታዊ ትንተና ስልት ተብራርተዋል። በዚህም መሠረት ማህበራዊ ፍትህን ለማጎልበት የሚያግዙ ሰባት የልማት አካሄዶች የተለዩ ሲሆን እነዚህም፡- የሀገር በቀል እውቀትን በልማት ማሳለጥ፣ ማህበረሰብን በትምህርት ማብቃት፣ ጎጂ ልማዶችን መዋጋት፣ ማህበራዊ ግንኙነትን ማጠናከር፣ ለአገራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነት ቅድሚያ መስጠት፣ ተተኪውን ትውልድ በመልካም ሥነምግባር ማብቃት፣ እና የሀገር ጠላቶችን እና አላማቸውን መለየት ናቸው። በመጨረሻም አገራት የዜጎቻቸውን ዕጣ ፈንታ ለመወሰን፣ አገራዊ ጥቅምና ክብራቸውን ለማስጠበቅ እና እንደአገር መቀጠል ካለባቸው ከነዚህ የልማት አካሄዶች መማር መተኪያ ሌለው አማራጭ እንደሆነ ከድራማው ትምህርት ሊቀስሙ እንደሚገባ ጥናቱ ጠቁሟል። በመጨረሻም የጥናቱ አንድምታዎችና ሊሄድባቸው ያልቻላቸውን ጉዳዮች በመጠቆም፣ ተጨማሪ ጥናቶች ሊካሄዱ እንደሚገባ ፍላጎቱ ላላቸው ተመራማሪዎች ጥሪው ቀርቧል።
Language: English
Open Access status: green
OpenAlex ID: W7128906406
FWCI:
Cites:
Cited by:
Related to: