የመቻቻል እሴቶች በደቡብ ወሎ ዞን ቃል-ግጥሞች ማሳያነት
Year: 2026
Type: article
Abstract: የዚህ ጥናት ዓላማ በማህበረሰባችን በጣም የተለመዱ ቃል-ግጥሞችን እንዴት የመቻቻል፣ አብሮ የመኖርና የመከባበር ስነ-አእምሯዊ ፍልስፍናዎችን ሲያስተላለልፍ እንደኖረና ይህም ለአብሮነታችን ያለውን አስተዋጽኦ ማሳየት ነው፡፡ ቃል-ግጥሞቹ ከ2011 እስከ 2016 ለስድስት ዓመታት ከተለያዩ የደቡብ ወሎ ዞን ወረዳ ማህበረሰቦች የተሰበሰቡ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በታላሚ ንሞና ዘዴ የተመረጡ 40 ቃል-ግጥሞች አገልግሎት ላይ ውለዋል፤ የማህበረሰቡን የወል ትርጉም በቃለ-መጠይቅና በውይይት ለመዘገብ ተሞክሯል፡፡ ቃል-ግጥሞቹ በጣም ጥልቅና በሳል መልእክቶችን የያዙ እና ማህበራዊ እሴቶችን የሚያስተላልፉ ሲሆን ከሃይማኖታዊ የጋራ እሴቶች (ሃይማኖተኝነት፣ ሰላማዊነት፣ አብሮነት፣ መከባበር፣ እውነተኛነት፣ ፍትሀዊነት፣ ይቅርታ፣ ሰብአዊ ርህራሄና በጎነት) አንጻር በስምንት ተመድበው ማህበረሰባችን የኖረበትን ስነ-አዕምሯዊ ትምህርቶችን ከዘመን ዘመን ሲያስተላልፉና ማህበረሰባችን ተቻችሎ፣ ተከባብሮና ተዋዶ በሠላምና በአንድነት እንዲኖር እንዳደረጉ ተመልክቷል፡፡ እነዚህ የቃል- ግጥሞች ማህበረሰቡን በሰላምና በአንድነት እንዲኖር አስችለውት የነበሩ ሲሆኑ እነዚህን ሀገር በቀል እውቀቶች ማህበረሰቡ እንዲያውቃቸው፣ እንዲረዳቸውና እንደገና መልሶ ዋጋ እንዲሰጣቸው ማድረግ የማህበረሰባችንን ወቅታዊ ችግር ለመፍታትና ሰላማችንን ለማስመለስ እንደሚረዱ በጥናቱ ተመልክቷል፡፡
Authors: ሰኢድ, ሙሐመድ, ከድር, አብዱልሃሚድ
Language: English
Topic: Language and Culture
Subfield: Linguistics and Language
Field: Social Sciences
Domain: Social Sciences
Open Access status: green
OpenAlex ID: W7128950931
FWCI:
Cites:
Cited by:
Related to:
